Monday, September 21, 2009

Truth Revealed !

የፊኔክስ አፍንጫ የብሽቀታቸው መለኪያ ወይስ….?
ፊኔክስ ትልቅ እና ግርማ ሞገስ ያለው ሀውልት ሲሆን የሚገኘውም የንጉስ ካፍሬ መቃብር የሆነው ፒራሚድ አቅራቢያ ነው። የጥንታዊ ግብፅ ታሪክ ተመራማሪዎች እንደሚሉት ፊኔክስ የራሱ የንጉስ ካፍሬ በድንጋይ ላይ የተቀጸ ምስል ነው። ፊኔክስ ስፋቱ 73 ሜትር ሲሆን የቁመቱ ከፍታ ደግሞ 20ሜትር ነው። ፊኔክስ ሃውልት ራሱ እና ሰውነቱ ወጥ ከሆነ ቦሀ ድንጋይ ተፈልፍሎ በሚያስደንቅ ጥበብ የተሰራ ነው።
ፊኔክስ ከአንገት በላይ የሰው ምስል ሲይዝ ከወገብ በታች ደግሞ የአንበሳ ምስል ነው ።ታዲያ የቀድሞ ጎብኝዎቹን እርር ድብን ያደረገው መች ግማሽ አካል አንበሳ መሆኑ ሆነና መልኩ እና አፍንጫው እንጂ ። ፍኔክስ የተሰራው እኛን በመሰሉ ሰዎች ብቻ ሳይሆን የንጉስ ካፍሬ እራሳቸው ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ነው። ሃውልቱ የንጉሱን ማንነት ፍንትው አድርጎ ነበር ያወጣው በተለይ አፍንጫና ከንፈራችው የኛን መስሎ የጎብኚዎቹን አልመስል ስላለ እንዴት እንዲህ ያለ ድንቅ ነገር እንዚህን በመሰሉ ሰዎች ይሰራል በሚል ዘረኝነትን ባዘለ ንዴት ሃውልቱን ላይ ያለውን አፍንጫ እና ከንፈር የድማሚት እራት አደረጉት።



ስለዚህም ሲነሳ እጆች ቶሎ የሚቀሰሩት ወደ ፈረንሳዊ ንጉስ ናፖሊዎን ቦናፔቲ ነው። በ1798 የቦናፔቲ ወታደሮች በመድፍ የፊኔክስን አፍንጫ ና ከንፈር እንዳፈረሱት ይነገራል። በቅርብ ሀውልቱ ላይ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት አፍንጫ እና ከንፈሩን ለማፍረስ ተቀጣጣይ ድማሚት በአፍንጫው ስር ተቀብረው እንደነበር ተደርሶበታል። ፈረንሳዎቹ ለምን እኛ ብቻ በሚል ይመስል እንግሊዞቹ በአንደኛው እና በሁለተኛው አለም ጦርነት በጥይት ተኩሰው ነው አፍንጫውን ያፈረሱት ይላሉ። መለስ ብለው ደግሞ ጀርመኖችም በሁለተኛው የአለም ጦርነት የተኩስ ልምምድ ሲያደርጉ እንደ ኢላማ የተጠቀሙት የፊኔክስን አፍንጫን ነው ይላሉ።ሌላም ደግሞ የተለየ ጨዋታ አላቸው በ693 የአረብ ተስፋፊዎች ናቸው ያፈረሱት ሲሉ አንዳንድ የአረብ ጸሃፍት ደግሞ በ1378 ቱርኮች ሃውልቱን እንደተመለከቱ ቱግ ብለው ይሄ ከእስልምና ጋር አይሄድም የሚል ሰበብ ፈልገው ነው ያፈረሱት ይላሉ።

ጥንታዊ ግብጻውያን ኢትዮጵያውን ለመሆናችው እሰጣገባ ውስጥ አያስገባንም ምክንያቱም የተጻፈን ታሪክ በማወቅ እና ባለማወቅ ላይ የሚደረግ ክርክር ስለሚያደርገው። ኢትዮጵያውያን በትክክል የጥንታዊ ግብጽ ስልጥኔ ላይ እና ፒራሚዶች ላይ ከፍተኛ አሻራቸውን ትተው አልፈዋል የሚለው እውነታ ሰርተው ያልፉት ሃውልቶች ህያው ምስክሮች ናቸው። በተለይ የአንድን ኢትዮጵያዊ መለያ መንገዶች መልኩ አይኑ አፍንጫው እና ከንፈሮቹ ናቸው ይህን ሆን ብሎ ማፍረስ ብሎም ማጥፋት ፒራሚዶች እና ሃውልቶቹ በኢትዮጵያውያን ንጉሶች አልተሰሩም እንደማለት ይቆጠራል።

አብዛኞቹ ተመራማሪዎች እንደ ሚስማሙት ከናፖሊዮን ግዜ ጅምሮ ነው ጥንታዊ ግብጽ ላይ በነገሱ ኢትዮጵያውያን ላይ ጠላቶች የተነሱት ይላሉ። ለዚህም ማሳያ የሚጠቅሱት ፊኔክስ የንጉስ ካፍሬ ሃውልትን ጨምሮ በጊዜው የነበሩት ኢትዮጵያውን ፈርኦኖች ወይም ንጉሶች ለራሳቸው መታሰቢያ ያሰሩት ሀውልቶች ከጭፍን ጥላቻ እና ዘረኝነት በመነሳት ሲያፈርሷቸው እና ሲያበላሿቸው ይስተዋላል።


ከዚህ በታች ያሉት ፎቶዎች ኢትዮጵያዊ መልክ ያላቸው ሀውልቶች ላይ የደረሱ ተመሳሳይ ጥፋቶች አጋልጠዋል።

ፈርኦን ሆትፕሲካሚ


ራምሴስ ሁለተኛ


ንጉስ አመንህመት ሶስተኛ [ባለ ሹሩባው ፈርኦን]


በጥንቱ ግብጻውያን ስርዎ መንግስት የነበሩ አዛውንት ምስል




እስኪ እራሳችንን እንጠይቅ ስለ የጥንታዊ ግብጻውያን በተለያዩ የብዙሃን መገናኛዎች ይነገራል ለምሳሌ ስለ ስልጣኔያቸው፤ የቀመር ችሎታቸው፤ ቋንቋቸው፤ ፊደላቸው [ሄሮግራፊክስ]፤ቀደምት አስደናቂ የወረቀት ስራቸው[ፓፒረስ]፤ ፒራሚዶቻቸው፤ አቻ ያልተገኘለት የግንባታ ጥበባቸው፤ ግዙፍ መቃብሮቻቸው፤ እምነታቸው ፤ ብዙ ብዙ ነገር ተጽፏል የቀረው ግን ዘራቸው ብቻ ነው። ለመሆኑ ጥንታዊ ግብጻውያን ከየት መጡ መነሻቸው ከየት ነው ?ዘራቸው ምንድ ነው? ? ነጮች ናቸው? አረቦች ናቸው? የሩቅ ምስራቅ ሰዎች ናቸው? የሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ ሰዎች ናቸው? አፍሪካውያን ናቸው? ለምን ይሆን ጥንታዊ ግብጻውያን ዘር እና መልክ ያልተገለጸው? ? ? ? ? ? ? ? ? ? ? አስቡት ፒራሚድ በነጮች ቢሰራ ምን ይሉ ነበር? እንዲህ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ይቀመጡ ነበር? ? ? ነጮች እና የሩቅ ምስራቅ ሰዎች እንዳልሆኑ ማንም ያውቃል አረቦችም ቢሆኑ አፋቸውን ሞልተው እኛ ነን ጥንታዊ ግብጻውያን ሊሉ አልደፈሩም ምክንያቱም አሌግዛንድሪያ እና ካይሮ ዛሬ አረባዊ ከተሞች ናቸው ከታሪካዊዎቹ ቦታዎች ጋር ምንም አይነት ይህ ነው ይሚባል ግንኙነት እንኳን የላቸውም ስለዚህ ዝምታን ይመርጣሉ።

ተመራማሪዎቹ ስለ ኢትዮጵያውያኖቹ ፈርኦኖች ግብጽን መግዛታቸውን ለመቀበል ይቅርና እንኳን ተሳስተው ለማውራት አይፈልጉም እውነቱ ግን በደግነታቸው እና በሩህሩነታቸው የሚታወቁት ኢትዮጵያውያን ፈርኦኖች ምስላቸውን ሳይቀር አስቀርጸው አልፈዋል። በጣም የሚገርመው ስለ ፒራሚዶች ጥናት መደረግ ከተጀመርበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ደረስ ስለ ግብጻውያን ዘር ትንፍሽ ለማለት የሞከረ የለም።
ፒራሚድን በተመለከት አይን ያወጣ ሻጥር እና ዘረኝነት ተስተውሎበታል እውነቱንም ለመደበቅ እጅግ በጣም ተሞክሯል። ነገር ግን የሞት ሞታቸውን በ2008 ናሽናል ጂኦግራፊክ ሶሳይቲ የሚባል የምርምር ጥናቶችን አሳታሚ መጽሄት ላይ ፈርኦኖችን ዘር በተመለከት ጥናታዊ ጽሁፍ ለማቅረብ በቅተዋል ምነው ይሄ ሁሉ ጊዜ ወሰደባቸው ? ? ? ነገር ግን ኢትዮጵያውያን የምትለው ስም ስላልተዋጠላቸው ወይም መጥራት ስላልፈልጉ ይመስል ከዚህ ሁሉ አመት ከፈጀ ጥናት በሃላ በመጽሄቱ ላይ ጥቁር አፍሪካውያን ሲያሻቸው ድግሞ ኩሽ እያሉ ጽፈዋል የሆነው ይሁን ፒራሚዶች እኛን በመሰሉ ሰዎች መሰራቸውን ማመናቸው በራሱ ትልቅ እመርታ ነው ።

http://ngm.nationalgeographic.com/geopedia/Black_Pharaohs

ሌላ ለአስረጂነት ያህል በጥንታውያን ግብጻውያውን የሚፈጸሙት ልማዳዊ ድርጊቶች ወይም እሴቶቻቸው በተለያዮ የምእራብያውያን እና አረብ ታሪክ ተመራማሪዎች እና ጻህፍት “የተለየ” ውይም “ያልተለመደ” ድርጊት የሚሉት ነው። እኛ ኢትዮጵያውያን የምናከናውናቸው ልማዳዊ ድርጊቶች ጋር አንድነት አላቸው ለምሳሌ መገረዝ፣ የንጉሶችን ስዮመ እግዚአብሄርነትን መቀበል፣ የእናትን ድርሻ መውረስ፣ ጥሎሽ፣ የተለያዮ ክብረ በአሎች፣ የቀብር ስነ ስርአቶች እነዚህ በትንሹ የተገለጹትን ልማዳዊ ድርጊቶች በአለም ላይ የሚፈጽሙት ኢትዮጵያውያን እና አፍሪካውያን ብቻ ናቸው።በምእራብያውያን እና አረቦች ሻጥር የጥንታውያን ግብጾች ኢትዮጵያዊ ባህሪ እንዲደበቅ ያሁኖቹ ተመራማሪዎች አበክረው ይሰራሉ። የኢትዮጵያውያን ንግስናን በጥንታዊ ግብጽ መኖሩን ባይቀበሉም ቅሉ ግን ቅን የሆኑ የታሪክ ተመራማሪዎን እኛ በግብጽ መንገሳችንን ከነማስረጃው አስደግፈው ጽፈዋል መጽሃፎቹን ማንበብ እና እውነቱን መረዳት ግን የኛ ፋንታ ይሆናል።

ከጥንታውያን ጻህፍት መካከል

Herodotus Origins of the Oracle of Dodona-book II
Aristotle-Physiognomy'' 6
Diodorus of SicilyOrigins of the Egyptians ''The Ethiopians say that the Egyptians are one of their colonies”-Universal History, book III
ከቅርቦቹ ተመራማሪዎች መካከል

Wonderful Ethiopians of the Ancient Cushite Empire
By Drusilla Dunjee Houston
Monuments from Egypt and Ethiopia by Karl Richard Lepsius (German: "Denkmaler aus Agypten und Athiopian")
Ethiopia and the origin of Civilization-A Critical Review of the Evidence of Archaeology, Anthropology, History and Comparative Religion: According to the Most Reliable Sources and Authorities by John G. Jackson (1939)

“አንድ ፎቶ ከአስር ሺህ ቃላቶች ይልቃል” እንዲሉ ከዚህ በታች ያሉት ፎቶዎች ኢትዮጵያዊ መልክ ያላቸው ንጉሶች እና ፈርኦኖች ናቸው ተመልከቷቸው።



ንጉስ ናይማሬ አመንህመት በሁለተኛው ስርዎ መንግስት



ንጉስ ቱቱናካሙን [በመቃብር ውስጥ የተገኘ]







ንግስት ጥዬ/ትዬ [የንጉስ ቱቱ እናት]



ፈርኦን መንኩራ [ሶስተኛው ስርዎ መንግስት]



ንጉስ ዩስካፌ




ፈርኦን ጆሴር



ንግስት ሃትሸብሱት



ፈርኦን ፐሪ አንኩ




የጥንት ግብጻዊ ቄስ


ግብጻዊ ቄስ በሁለተኛው ስርዎ መንግስት