Saturday, March 12, 2011

ቼርኖቤል የኒውክለር ማብለያ ጣቢያ ድንገተኛ አደጋ።


ቼርኖቤል በቀድሞ ሶቭየት ህብረት አካል የነበረች በዮክሬን ግዛት ውስጥ የምትገኝ የሃይል ማመንጫ ጣቢያ ናት። ከፕሪፒያት ከተማ በ3ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተተከለው ቼርኖቤል ኒውክለርን በመጠቀም የኤለክትሪክ ሃይል የሚያመነጭ ጣቢያ ነው። አርብ ሚያዝያ 18,1978 አ.ም. እኩለ ሌሊት በቼርኖቤል ኒውክለር ማብለያ ጣቢያ ውስጥ በደረሰው ፍንዳታ የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ሰጪዎችን እና ተመራማሪዎችን ጨምሮ ለአራት ሺህ ሰዎች ህይወት መጥፊያ ሲሆን ከሶስት መቶ ሰላሳ ስድስት ሺህ ሰዎች በላይ ለመፈናቀል ምክንያት ሆኗል። የፍንዳታው ውጤት ሶቭየት ህብረት፤ ምስራቅ ፤ምእራብ እና ሰሜን አውሮፓን አጥቅቷል። በይበልጥ የችግሩ ሰለባ የሆኑት ዮክሬን ቤላሩስ ራሺያ ነዋሪዎች ነበሩ። የደረሰውን አደጋ በቁጥጥር ስር ለማዋል ባሁኑ ገንዘባችን ሲሰላ አንድ ትሪሊዮን አንድ መቶ ሃያ አምስት ሚሊዮን ብር ፈጅቶአል።

በደረሰው ፍንዳታ የተመረዘውን ቦታ በፍጹም ማጽዳት የማይቻል ሲሆን። ጣቢያው የተተከለበት ህንጻ ዙርያውን መጠኑ ተወዳዳሪ በማይገኝለት ወፍራም ግንብ ታሽጓል። ነገር ግን የታሸገበት ግንብ ለሰላሳ አመት ድረስ ያህል እንዲያገለግል ሆኖ ነው የተሰራው። አሁን አደጋው ከደረሰ ከሃያ አመት በላይ ሆኖታል። በኒውክለር ጨረር የተመረዙ ሰዎች እና የሚወልዱት ልጆቻቸው የአደጋው ሰለባ መሆናቸውን ግን እስካሁን አላቋረጡም።

“…ቼርኖቤል የኒውክለር ሃይል በሰዎች እጅ ሲገባ እንዴት እንደሆነ ሃይሉን አሳይቶናል። እኛ ያሉንን ኤስ ኤስ 18 ሚሳኤሎቻችንን ስናሰላቸው እያንዳንዱ ከመቶ ቼርኖቤል በላይ ሃይል ያላቸው ናቸው። ኤስ ኤስ 18ትን አሜሪካውያን ከምንም በላይ የሚፈሩት የጦር ሚሳኤል ነው። እኛ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ የሚሆኑ አሉን። እነዚህ ሚሳኤሎች እኛ ለአሜሪውያኑ ብለን የሰራናቸው ናቸው። ሁለት ሺህ ሰባት መቶ አስቡት ሊያመጡት የሚችሉት ጥፋት።…”

-----ሚካኤል ጎርቫቾቭ የቀድሞ የሶቪየት ህብረት ፕሬዘዳንት እና የሶቪት ህብረት ኮሚኒስት ፓርቲ ዋና ጸሃፊ










Tuesday, March 8, 2011

የብርሃኔ እናት የደስታ እናት አልማዝዬ ናት።

ይህ ዘፈን የቆየ ቢሆንም እጅግ በጣም ደስ የሚል ለዛ ያለው ነው። በተለይ ወንድም እና እህት ወይም አክስት እና አጎት እንጂ ባል እና ሚስት የማይመስሉት አባት እና እናቶቻችንን በጣም የሚገልጽ ነው። አባቶቻችንን እና እናቶቻችንን ፍጽም ተወዳዳሪ የሌላቸው ጨዋዎች እና ሰው አክባሪዎች መሆናቸውን ከዚህ ዘፈን መረዳት ይቻላል። ይህም ዘፈን ጨዋነት በተሞላ ለዛ ሲጫወቱት ደስ ይላል። በባህላችን የራሳችን የትዳር ጓደኛችንን የምናሞስበት ዘፈን እንዳለን ያመላክታል።

Monday, January 17, 2011

የኪንግ ታሪክ እና የ፪፭ኛ አመት አገልግሎት እዮቤልዮን የሚመለከት ታሪክን የሚዳስስ ጥንቅር::


ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ የታሪክን ሂደት የለወጠበት እና “የወገን ፍቅር “ የሚለውን ሃሳቡን ብዙ ሰዎች በከፍተኛ ተነሳሽነት የገነቡበት ነው። የኪንግ ታሪክ እና የ፪፭ኛ አመት አገልግሎት እዮቤልዮን የሚመለከት ታሪክን የሚዳስስ ጥንቅር እንዴት የዶክተር ኪንግ ልደት ወደ ብሄራዊ የአገልግሎት ቀን እንደተሸጋገረ ያሳያል። የሰበአዊ መብት ፋናወጊ የሆኑት ኮንግረስ አባል ጆን ሌዊስ ፤ ሬቭረንድ ዶክተር ጆሴፍ ሎወሪ እና ሩቢ ብሪጅ ተካተውበታል። ይህ ስድስት ደቂቃ የፈጀ ዝግጅት የዶክተር ኪንግን ታሪክ መዘከር ጠቀሜታው ወገንን ማገልገል የበለጠ መነቃቃትን እንዲፈጥር እና ለወገን እና ለህብረተሰብ አገልግሎት አመቱን ሙሉ በማንኛውም ቀን እንድንሰጥ ዝግጁነታችንን በበለጠ ያጠናክራል።