ሰላም ነው!!!
ሰላም ነው እንዴት ነው? ይመስገን ይህን ታህል አልን ፤ይህ ሳምንት በጣም አስገርሞኝ እንድተነፍስላችሁ የዳዳኝ ነገር ቢኖር "የሰላም ነው" ነገር ነው ።ጓደኞቼንም ሆነ ማንኛውንም ሰው ሰላም ማለት ከጀመርኩበት ግዜ ጀምሮ አፌ ላይ የሚመጣው የሰላምታ አሰጣጥ ሰላም ነው !! የሚለው የሰላምታ አሰጣጥ አይነት ነው። ለማውቀው ሰው ሁሉ ነው የምለው ምናልባት በእድሜ ለገፉ ሰዎች ወይም እንግዶች እና አክብሮት በሞያችው ለሚቸራቸው ሰዎች ካልሆን በቀር በየጊዜው የማገኘውን ሰው ሁሉ የምለው ሰላም ነው!!! ነው ታዲያ በዚህ ሳምንት ውስጥ ነው አብሮኝ የሚሰራ አማርኛ ተናጋሪ ሰው አለ ታዲያ ይህ ሰው በጨዋታ መሃል ሰላም ነው የሚለው ሰላምታ አሰጣጥ በቅርብ ጊዜ የተለመደ እንደሆን አስረግጦ ነገረኝ ፤ ባይገርማችሁ እንደዚህ አይነት ነገር ሲያጋጥምኝ የመጀመሪያዬ ነው በእሱ አባባል የዚህ ትውልድ ልጆች ናችሁ ይህንን "ሰላም ነው" የሚለውን የስላምታ አሰጣጥ የምትከተሉት አለኝ በርግጥ እኔ ከዚህ ትውልድ በፊት ስላልነበርኩኝ ስለ ድሮ ሰላምታ አስጣጥ ይህ ነው ብዬ የምለው ነገር የለም ነገር ግን በርግጠኝነት የምናገረው ነገር ቢኖር "ሰላም ነው" የሚለው ሰላምታ አስጣጥ በጣም የተለመደ መሆኑን ነው እስኪ እርሶ የሰላምታ እሰጣጦቻችን ላይ ያለዎትን አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ አስተያየት በግርጌ ማስታወሻ ላይ ያስፍሩ መልካም የስራ ሳምንት።
No comments:
Post a Comment