Wednesday, June 24, 2009

የስምዎ ቁጥር ስንት ነው?

        የቋንቋዎች ሁሉ አባት በሆነው ግእዝ ፊደላት አኅዛዊ መጠን አላቸው ።ስለዚህ ከፊደሎቹ ቁጥር በመነሳት እያንዳችን ስም ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ ማወቅ ያስችለናል  ። የስም ቁጥር  በመጻህፍ ቅዱስ ውስጥ በዩሃንስ እራይ " የስሙም ቁጥር ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት ነው" ተብሎ እራሳችንን ከአውሬው ቁጥር ነቅተን እንድንጠብቅ ታዘናል ። ስለዚህ ዛሬ ሁላችንም የስማችንን ቁጥር ልክ እንወቀው፤ አቆጣጠሩ በጣም ቀላል ነው። በመጀመርያ እያንዳንዱ የስማችንን ፊደል ወደ ፊደሉ መነሻ ፊደል መውሰድ ነው። ለምሳሌ 'ዳ'ን ወደ 'ደ' 'ም'ን ወደ 'መ' ፤ በመቀጠል ከግርጌ በኩል  ወደ ተቀመጠው ሰንጠርዥ በመውረድ የእያንዳንዱን ፊደል አሃዙን ካወቅን በሃላ አንድ ላይ እንደምረዋልን።

ለምሳሌ አዳም የሚለውን ስም ቁጥር በግእዝ አኅዛዊ መጠን ላይ በንመለከተው

አ = 40

ደ = 100

መ = 4

በጠቅላላ = 144  ይሆናል ማለት ነው እስቲ እርሶም ከዚህ በታች በተቀመጠው ሰንጠርዥ በመጠቀም የስምዎን ቁጥር ይፈልጉ።

No comments: