Wednesday, July 1, 2009


አክሱም ጺዩን በአንደበታቸው



በአለም ላይ ይህ እጅግ በጣም የሚፈራ እና ድንቅ ተአምራትን የሚሰራው ታቦተ ህግ ለብዙ ሺህ አመታት ተጠብቆ የሚገኘው አክሱም ጺዮን ውስጥ መሆኑን በልበ ሙሉነት የምትናገረው ኢትዩጵያ ብቻ ብትሆንም የቀድሞ ባለቤቶቿ ግን ፈጽሞ ሊዋጥላቸው አልቻልም በርግጥም ጺዮን ለምን ለኢትዩጵያ እና ለኢትዩጵያውያን እንደማይገባን ሲናገሩም አይደመጡም ?... አሁንም ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ታቦተ ጺዮንን ፍለጋ የማወጡት ተራራ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም ። እንደ እነ ኢንዲያና ጆን የመሳሰሉ የሆሊውድ ተረቶችን ጨምሮ ልፋ ያለው …..


እንዴት ተደርጎ ወደ ኢትዩጵያ ውስጥ ይገባል፣ የማይሆን ነገር ነው፣ አፈ ታሪክ ነው፣ ሳባ አረብ ናት፣ቀዳማዊ ሚኒልክ የኢትዩጵያውያን ፈጠራ ነው ሲሉ ይቆዩኑና አይናቸውን በጨው አጥበው ደግሞ ትግራይ ነው ያለው፣ መጀመርያ ያረፈው ጣና ደሴት ላይ ነው አብረው የመጡትም እዛው ተቀብረዋል፣ ትክክልኛዋ ጺዩን እንዳትታወቅ 50000 ተመሳሳይ ጽላቶችን ሰርተዋል ፣ በደናግላን ነው የምትጠበቀው ይሉናል። እንደገና ይመለሱ እና እውን ታቦተ ጺዩን በኢትዩጵያውያን እጅ ከሆነች ለምን በድርቅ፣ በረሃብ፣ በበሽታ፣ብስደት፣በርስ በርስ ጦርነት፣በዘርኝነት፣በጎጥኝነት፣ በመልካም አስትዳደር እጦት ይሰቃያሉ ይላሉ ። ወዲያው ይመለሱ እና እንደ ኢትዩጵያውያን ጠላቶች መብዛት፣ እና እስካሁን እንደ ተሳተፉበት ጦርነት ቢሆን ኖሮ ካለ ታቦተ ጺዩን ጠባቂነት ኢትዩጵያ እንደ ሃገር እዚህ ምድር ላይ አትኖርም ነበር መሬት መንቀጥቀጥ አያውቁ፣ቶርኔቶ አያውቁ፣ሱናሚ አያውቁ፣ ብለው ይሉናል።


እንድገና ሌላ ጨዋታ ይጀምራሉ የጽላቱ ሃይል በምድር ላይ የሚያክለው የለም፣ በጦር ሜዳ ላይ በቅጽበት ድልን ያቀዳጃል፣ የዚህን ሀይል የሚለካ መሳሪያ የለንም፣ ከኒውክለር ይበልጣል ሲሉ ይቆዩና፣ ተመልሰው ጽላቱን በአይናችን እንየው፣ ብእጃችን እንንካው፣በአይናችን እንድናይ እስካልተፈቀደልን ድረስ ጽላቱ በኢትዮጵያ ውስጥ መኖሩን አንቀበልም አሁን ደግሞ ሙዝየም ውስጥ ይቀመጥልን እያሉ ባግኙት አጋጣሚ ሁሉ ይውተውታሉ ፣ አንዳንዴማ ጆሮ አይሰማው የለ አይን አያየው የለ እነዚህ ሰዎች በጤናቸው ነው ያስብላል።


ምናልባት ይህንን ሙሴ ከእግዚአብሔር በሲና ተራራ የተቀበለው ታቦተ ህግ በኢትዬጵያ አክሱም ጺዮን ውስጥ እንደሚገኝ በማስረጃ የተደገፈ ግኝት በተከታታይ አራት ክፍል ቀርቦ ሲመለከቱት ምናልባት ከተምታታበት ሃሳባቸውን ፈቅ ሊሉ ይችሉ ይሆናል እርሶም በጽሞና ይከታትሉት ።

No comments: